Blog
srdtb
Subscribe:.rss.atom.json.md
Live Last read · last published · next check
Latest posts

በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለከተማ ታክሲ ትራንስፖርት ጊዜያዊ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለፀ :: በሀገር ደረጃ ያጋጠመውን የታርጋ እጥረትን መነሻ በማድረግ በክልሉ በሐዋሳ ከተማ እና በዞን ከተሞች የኤሌክትሪክ ታክሲ እንዲሁም ኩይት ተሽከርካሪዎችን በመግዛት በመንግስት በኩል ምላሽ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ እንደሆነ በመድረኩ በቢሮ ኃላፊ ተገልፆዋል:: ለዚህም ምላሽ ከቢሮ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ጨምሮ አብራርቷል :: ቢሮው እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በጋራ በመሆን ባደረገው ጥረት ጊዜያዊ የስምሪት ኮድ ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት መስጠት…

በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ቡድን በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ካሉት ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ጋር የዞን አመራሮች ባሉበት ምክክር ተደርጓል:: በምክክር መድረኩ በዞን ደረጃ እየተሰሩ የሚገኘው የግንባታ እና ጥገና መንገዶች እንዲሁም የድልድይና እስትራክቸር ስራዎች አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ ተገምግሟል:: ኮንትራክተሮቹ ከነዳጅ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች ከተቀረፈላቸው ፕሮጀክቶቹን በተባለው ጊዜ ዉስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል:: የፕሮጀክቶች አፈፃፀም በጥራት አጠናቆ ከማስረከብ አንፃር የሚታዩ ችግሮች ; የኮንትራክተሮች የአፈፃፀም ፍጥነት ጊዜን ታሳቢ በማድረግ ከመስራት ረገድ…

የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ዉጤት እያመጣ እንደሆነ ተገለፀ:: በሲዳማ ክልል የመናኸሪያዎች አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ በመደረጉ አገልግሎቱን ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡ በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራዉ የጉብኝት ቡድን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአዲሱ እና በአሮጌ መናኃሪያዎች ተገኝተዉ የአገልግሎት አሰጣጡን ሂደት ምልክታ አድርገዋል፡፡ ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጡ ሂደት የሚታዩ ችግሮች እንዲፈቱ ቢሮዉ በክልሉ የሲዳማ ዲጂታል ትራንስፖርትን መመሪያ በማዘጋጀት ተግባራዊ እያደረገ በመሆኑ በትራንስፖርት በኩል የሚታዩ ችግሮች እንዲፈቱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ…

የመንገድ ልማት ሥራዎች ለህዝባችን የደም ሥር ናቸው:: ሴክተሩ በገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና (RCFSP) ፕሮግራም አማካይነት የተለገሱ 7 ያማሀ ሞተር ሳይክሎችን በፕሮጀክቱ ለሚደገፋ 7 ወረዳዎች የርክክብ መርሀ- ግብር አከናውኗል:: የቢሮ ሀላፊው አቶ ጎሳዬ ጎዳና ለወረዳ ፅ/ቤት ሀላፊዎች የቁልፍ ርክክብ ሥነ- ሥርዓት ሲያደርጉ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል:: ይህ በፕሮጀክቱ አማካይነት ከፌዴራል መንግስት ያገኘናቸው 2 ሀርድ ቶፕ መኪናዎች፣ 7 ሞተር ሳይክሎች የ100 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀምን ግብረ- መልስ እየሰጠን ባለንበት ወቅት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል:: የፕሮጀክቱ ድጋፍ የመንገድ ልማት…

በሲዳማ ክልል የመንገድ ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ:: በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ እና ማዕከላዊ ሲዳማ ዞኖች በቢሮ በኩል ግንባታቸው እየተከናውኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በቢሮ ኃላፊ በአቶ ጎሳዬ ጎዳና በተመራው ቡድን ምልከታ ተደርጓል:: በሪካፕ ፕሮግራም በኩል የጥገና ሥራ ተጠቃሎ ሪክክብ የተደረገዉ በጎርቼ ወረድ የሚገኘ የዊጣ ጎርቼ ፕሮጀክት በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ለማየት ተችሏል:: በመንገዶች ባለስልጣን በኩል እየተገነባ የሚገኘው የዎላ ጃልዶ ቡሳዋ የ14 ኪሜ ማቴሪያል የመበተን ሥራ በጥሩ ሁኔታ ጥራቱ ተጠብቆ እየተሰራ ይገኛል:: መንገዱ የጎርቼ ሻፋሞ እና የአርቤጎና ወረዳዎችን የሚያገናኝ በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ…

በሲዳማ ክልል የዩራፕ ፕሮጀክቶች ዋጋ ማሻሻያ ጥናት ላይ ምክክር ተደረገ:: በሲዳማ ክልል በዩራፕ ዘርፍ በኩል ግንባታቸው በሚከናወኑ የመንገድ እና የድልድይ ግንባታዎች የዋጋ ማሻሻያ ጥናት ቀርቦ ምክክር ተደረገ :: በምክክር መድረኩ በጥናት ቡዱኑ ኮሚቴ አባላት በክልል ደረጃ ዋጋ ማሻሻያ ለማድረግ መሰረታዊ ምክንያት የሆኑ ጉድዮች ተለይቶ ጥናት እንደተደረገ ከቀረበዉ የጥናት ሠነድ ለማረጋገጥ ተችሏል:: በመድረኩ ተገኝተው የጥናቱን አስፈላጊነት በክልል ደረጃ ከክልሉ መንግስት ምክር ቤት አባላት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አባላት በተገኙበት ምክክር በማድረግ ፀድቆ በሥራ ላይ እንዲዉል ለማድረግ እንደሆነ የርዕሰ…

የአከባቢና ማህበራዊ ክዋኔ ኦዲት በተቀናጀ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ ተገለፀ:: በሲዳማ ክልል በRCFSP ፕሮግራም አተገባበር ዙሪያ በሲዳማ ክልል የአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን በኩል የ2017 በጀት ዓመት የአከባቢ እና ማህበራዊ ጉዳዮች አጠባበቅ ዙሪያ የተከናውኑ ተግባራት የክዋኔ ኦዲት ግምገም ሪፖርት የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና በተገኙበት ተገምግሟል:: ፕሮግራሙ በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግ በመሆኑ ሁሉም ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸው በመድረኩ ተገልጿል:: በግምገማው በቀረበዉ የክዋኔ ኦዲት የመንገዶች እና ስየአከባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን መንገዶችን ስፔሻል እስትራክቼሮች…

ከፌደራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን ጋር ምክክር ተደረገ:: በሲዳማ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የRCFSP ፕሮግራም አተገባበር ዙሪያ በክልሉ በፕሮግራሙ የታቀፉ የባለድርሻ አካላት በሙሉ በተገኙበት ከድጋፍ እና ክትትል ቡድን ጋር ውይይት ተደርጓል :: የድጋፍ እና ክትትል ቡድኑ በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን መነሻ በማድረግ የነበሩ ስኬቶች እና ያጋጠሙ ችግሮች ተለይቶ እንዲሁም የ2018 በጀት በሚሰሩ ፕሮጀክቶች አንፃር ትኩረት በማድረግ ሠነድ በድጋፍ እና ክትትል ቡድኑ ቀርቧል:: በመድረኩ የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት ፕሮግራሙ በክልላችን በ7…

ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳና የዘመነ የአመራርና ባለሙያዎች ትጋት ለተቋም ግንባታ ቁልፍ እንደሆነ ተገለፀ:: ለሴክተሩ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደዋል። ቢሮ ሀላፊው ሲናገሩ :- የቢሯችን አመራርና ባለሙያዎች ከብልሹ አሠራርና የሠራተኞችን አዋጅ ደንብና መመሪያን በአግባቡ ከመተግበር አንፃር ምን እንደምንመስል ራሳችንን ለመመልከት ይረዳን ዘንድ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቷል። አክለውም አቶ ጎሳዬ ይህ መድረክ ሁላችንም ብልሹ አሠራርን እንድንጠየፍና የሠራተኞች አዳዲስ የወጡ አዋጆች: ደንቦችና መመሪያዎች ያለንን ግንዛቤ በማሳድግና ግልፀኝነት በመፍጠር ድርሻው የጎላ…

ለተቋማት የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት የተሻለ ለውጥ ማስመዝገብ ይገባል። የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ከሴክተሩ አመራርና ባለሙያዎች ትውውቅ ጋር አድርገዋል። በትውውቅ መድረኩ የቢሮ ሀላፊው በመልዕክታቸው:- በቀጣይ የሚኖረን የስራ ዘመን ለተቋሙ የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት ተግባራትን ቀልጣፋ እናደርጋለን፣ ቀደም ሲል የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በማጎልበት ባሉት ጉድለቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ርብርብ ይደረጋል፣ የምንሠራው ሥራ ብዙሀንን ማከለ መሆን አለበት ብለዋል። አክለውም የተቋሙ ሠራተኞች ምቹ ውጤታማ ማድረግና ሠላማዊ የሆነ የሥራ ግንኙነት መፍጠር ይገባል። እንዲሁም ለባለሙያው የሥራ…