RSS Amplifier

Blog

Federal Ethics & Anti-Corruption Commission

Federal Ethics & Anti-Corruption Commission

feacc.gov.etSource feed ↗11 posts

Live Last read · last published · next check

Latest posts

የኩባንያው የቀድሞ ሊቀመንበር በሙስና ወንጀል የእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ

የቻይናው የንብረት ግዙፍ ኩባንያ ኤቨርግራንዴ የቀድሞ ሊቀመንበር ሹ ጂያይን በከባድ የገንዘብ ማጭበርበርና የሙስና ወንጀሎች ጥፋተኛ በመሆናቸው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው። የሼንዘን መካከለኛ የሕዝብ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ፣ የሹ ጂያይን የግል ንብረታቸው በሙሉ እንዲወረስ እና የፖለቲካ መብታቸውን በእድሜ ልክ እንዲነጠቅ፤ ከወንጀል የተገኙ ሕገወጥ ገቢዎች እንዲመለሱ እና ጉድለት ካለ እንዲሟላ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ እንዳረጋገጠው፣ ሹ ጂያይንና […]

17ኛው አገርዓቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ ተካሄደ

17ኛው አገርዓቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ ግምገማዊ ውይይት ተካሂዷል። አገርዓቀፍ የትስስር ጉባኤው በ2018 በጀት አመት በሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና ቅድመ-መከላከል፣ በተቋማዊ ማስፈጸም አቅም ግንባታ ጋር በተያያዘ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥና ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ ስምምነት በመፍጠር የተቀናጀ ዘርፍ ተኮር የፀረ-ሙስና ትግል […]

የፀረ-ሙስና ትግሉ የህዝብና የመንግሥት ቋሚ አጀንዳ ሆኖ መቀጠል አለበት – ምክትል አፈ ጉባዔ የተከበሩ ሎሚ በዶ

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በድምቀት አክብሯል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ሎሚ በዶ ዛሬ የምናከብረው የፀረ-ሙስና ትግል ያለፈውን ለመዘከር ብቻ ሳይሆን፣ ያለንበትን ለመገምገምና ወደፊት የምንመራበትን አቅጣጫ ለመወሰን የሚያስችለን ነው ብለዋል። በሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዋና መወያያ ነጥቦች መካከል ሙስና […]

በኮሚሽኑ በየአስራ አምስት ቀን የሚዘጋጀው የግንቦት ወር 2ኛ ዙር ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ

በኮሚሽኑ በየአስራ አምስት ቀን የሚዘጋጀው የግንቦት ወር 2ኛ ዙር ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ Download

ኢትዮጵያ በብሪክስ (BRICS) መድረክ አማካኝነት ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ትብብርን እያጠናከረች ነው

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኢትዮጵያን በመወከል በሃይደራባድ፣ ህንድ በተካሄደው ሁለተኛው የBRICS ፀረ-ሙስና የሥራ ቡድን (ACWG) ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ሙስናን ለመዋጋት በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ ያላትን ተሳትፎ አጠናክራለች። የBRICS አባል ሀገራት እና አጋሮች የውይይት መድረክ ሙስናን በመከላከል እና በመዋጋት ረገድ የተጠናከረ ትብብርን ለመወያየት፣ የህግ አስከባሪ ትብብርን በማጠናከር፣ ከሙስና ጋር የተያያዙ ወንጀኞችን በመከታተል እና የርክክብ […]

ETHIOPIA LAUNCHES HISTORIC NATIONAL DIALOGUE FEATURING CORRUPTION AND GOOD GOVERNANCE AS CORE AGENDA

ADDIS ABABA, ETHIOPIA — in a groundbreaking move for the region, Ethiopia has officially launched its first-of-its-kind National Dialogue, bringing together thousands of representatives to address the country’s most critical structural challenges. While traditional national dialogues globally focus almost exclusively on immediate political crises, Ethiopia’s 35-day session stands out on the world…

በኮሚሽኑ በየአስራ አምስት ቀን የሚዘጋጀው የሐምሌ ወር 1ኛ ዙር ፀረ-ሙስና ዲጂታል ጋዜጣ

ሐምሌ.15 Download

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ(ATC) ታወር ግንባታ ግዥ የጨረታ ሂደት ላይ የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ምክረ ሀሳብ አቀረበ

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ(ATC) ታወር ግንባታ ግዥ የጨረታ ሂደት ላይ የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል። ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1236/2013 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀፅ 4 መሠረት ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሲጠረጥር ወይም ጥቆማ ሲደርሰው ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ሂደቱ እንዲቋረጥ […]

የ325 ሚሊዮን ዶላር ጉቦ የተቀበሉት ባለሥልጣን ሞት ተፈረደባቸው

​(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም) በምስራቃዊ ቻይና የሚገኝ ፍርድ ቤት በ30 ዓመት ጊዜ ውስጥ 2.2 ቢሊዮን ዩዋን በላይ ወይም 325 ሚሊዮን ዶላር በሙስና በመቀበል የተከሰሱት የቀድሞ የከተማዋ አስተዳደር ባለሥልጣን ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈ። ቅጣቱ የተላለፈባቸው ያንግ ዩሊን ከአውሮፓውያኑ 1993 እስከ 2023 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ በናንጂንግ ከተማ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል ተብሏል። የቀድሞው ባለሥልጣን በማጭበርበር፣ ሥልጣንን አላግባብ […]

በኮሚሽኑ በየአስራ አምስት ቀን የሚዘጋጀው የሰኔ ወር 2018 ዓ.ም 2ኛ ዙር ዲጂታል የፀረ-ሙስና ጋዜጣ

ሰኔ 30-2018 ዓ.ም Download

ሙስናና ብልሹ አሰራርን ማስወገድ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና ይጫወታል – ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

***** (ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሂዷል። ስልጠናዊ ውይይቱ በሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ ተቋማት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝና አመራሮች የፀረ-ሙስና ትግሉን በባለቤትነት እንዲመሩ የሚያስችል ነው። በስልጠናው የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) […]